am_tn/psa/091/003.md

2.1 KiB

እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ደግሞም ከክፉ መቅሰፍት ያድንሃል

የተተዉት ቃላት ሊጨመሩ/ሊገቡ ይችላሉ፡፡ "እግዚአብሔር አንተን ከአዳኝ ወጥመድ እና ሊገድል ከሚችል መቅሰፍት ያድንሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

የአዳኝ ወጥመድ

"አዳኝ አንተን ለመያዝ ካስቀመጠው ወጥመድ"

በክንፎቹ ይጋርድሃል/ይሸፍንሃል፣ ከክንፊፎቹም በታች መሸሸጊያ ታገኛለህ

እዚህ ስፍራ የእግዚአብሔር ጥበቃ የተገለጸው ወፍ ጫጩቶቿን ከአደጋ እንደ ምትጋርድበት "ክንፎች" ተደርጎ ነው፡፡ "በክንፎቹ ይሸፍንሃል" እና "ከክንፎቹ በታች" የሚሉት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "እርሱ በሰላም ይጠብቅሃል፣ ይጋርድህማል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእርሱ ታማኝነት ጋሻ እና ጥበቃ ነው

እዚህ ስፍራ የእግዚአብሔር ታማኝነት የሚለው የተገለጸው በእርሱ የሚታመኑ ሰዎችን መጠበቅ እንደሚችል "ጋሻ" ተደርጎ ነው፡፡ "ታማኝነት" የሚለው ረቂቅ ስም "መታመን" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እርሱ እንደሚጠብቅህ ልትታመንበት ትችላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

መከላከያ

የዚህ ቃል ትርጉም በእርግጠኝነት አይታወቅም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ወታደሮች ራሳቸውን ከጠላት ቀስቶች እና ሰይፍ ለመከላከል በክንዳቸው የሚያዙት ትንሽ ጋሻ፤ ወይም 2) ወታደሮች በውስጡ ተሸሽገው ቀስት የሚወረውሩበት በክብ የተሰራ የድንጋይ ግርግዳ