am_tn/psa/091/001.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነ ግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻይ በሆነው …ዘንድ የሚኖር እርሱ…ያድራል

"መጠጊያ/መጠለያ" እና "ጥላ" እንደሚሉት ለጥበቃ ዘይቤያዊ አገላለጽ እንዳላቸው ቃላት ሁሉ "መኖር" እና "ማደር" የሚሉት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ስለዚህም ሁለቱን ስንኞች በአንድ ላይ ማጣመር ይቻላል፡፡ "እጅግ ከፍ ያለው እና ሁሉን ቻይ የሆነው በእርሱ ጥበቃ ውስጥ ለሚኖሩ ጥንቃቄ ያደርግላቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ጥንድ ትርጉም የሚሉትን ይመልከቱ)

እጅግ ከፍ ባለው መጠለያ/ በልዑል መጠጊያ የሚኖር

"መጠለያ" የሚለው ቃል ያህዌን የሚያመለክት ዘይቤ ነው፡፡"ልዑሉ ለእርሱ ጥበቃ በሚያደርግበት የሚኖር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እጅግ ከፍ ያለው /ልዑሉ

"ልዑል/እጅግ ከፍ ያለ" የሚለው ቃል ያህዌን ያመለክታል፡፡ ይህ በመዝሙር 18፡13 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ሁሉን ቻይ በሆነው ጥላ ስር ይቆያል/ያድራል

እዚህ ስፍራ "ጥላ" የሚለው ቃል ጥበቃ ለሚለው ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "ሁሉን ቻይ የሆነው ሊጠብቀው በሚችልበት ስፍራ ይቆያል/ያድራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻዩ

ሀይል ያለው እና ሁሉን ነገር ሊቆጣጠር/ሊገዛ የሚችል፡፡ ይህ በመዝሙር 68፡14 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ያህዌን እንዲህ እለዋለሁ

"ስለ ያህዌ እንዲህ እላለሁ"

መሸሸጊያዬ እና ምሽጌ

"መሸሸጊያ" አንድ ሰው ሊሄድ የሚችልበት እና የሚሸሽገው ሰው ወይም ነገር የሚያገኝበት ስፍራ ነው፡፡ "ምሽግ" ሰዎች ራሳቸውን እና ያላቸውን ንብረት ለመጠበቅ የሚያበጁት ስፍራ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ አሳፍ እነዚህን ለጥበቃ እንደ ዘይቤ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ "እኔ ልሄድ የምችልበት እና እርሱም እኔን የሚጠብቅበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚውን ይመልከቱ)