am_tn/psa/090/007.md

1.3 KiB

እኛ በቁጣህ አልቀናል

የሰዎች በእግዚአብሔር ቁጣ ማለቅ የተገለጸው፣ የእግዚአብሔር ቁጣ ሰዎችን ሙሉ ለሙሉ የሚያጠፋ እሳት እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ በቁጣህ አጠፋኸን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እኛ ከቁጣህ የተነሳ ተሸብረናል

"አንተ በምትቆጣ ጊዜ እኛ እጅግ እንፈራለን"

በደላችንን በፊትህ፣ የተሰወሩ ኃጢአቶቻችን በመገኘትህ ብርሃንህ ውስጥ አኖርክ

እግዚአብሔር የሰዎችን ኃጢአት መመልከቱ የተገለጸው፣ ኃጢአት በራሱ ፊት እንደሚያስቀምጠው ቁስ እና እንደሚመለከተው ነገር ተደርጎ ነው፡፡ "አንተ እኛ የምናደርጋቸውን ክፉ ነገሮች ሁሉ፣ በስውር ያደረግናቸውን እንኳን ሳይቀር ታያለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)