am_tn/psa/090/003.md

2.5 KiB

አንተ ሰውን ወደ አፈር ትመልሰዋለህ

ይህ የሚያመለክተው፣ እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ሰው፣ አዳምን፣ ከአፈር እንደፈጠረው፤ ሰዎች ከሞቱ በኋላ እግዚአብሔር የሰው አካል ወደ አፈር እንዲመለስ እንደሚያደርግ ነው፡፡ "አንተ ሰዎችን ሲሞቱ ወደ ትቢያነት ትመልሳቸዋለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰውን ትመልሰዋለህ

እዚህ ስፍራ "ሰው" የሚለው በአጠቃላይ የሰው ልጅን ነው፡፡ (ጡንቻማነትን የሚገልጹ ቃላት ሴትን ሲያካትቱ የሚለውን ይመልከቱ)

አናንተ ትውልዶች/የሰው ልጆች ትመለሳላችሁ

"ወደ ትቢያ" ወይም "ወደ አፈር" የሚሉት ቃላት በውስጠ ታዋቂነት ይገኛሉ፡፡ "አናንተ ትውልዶች ወደ ትቢያ ትመለሳላችሁ" ወይም "እናንተ ትውልዶች ወደ አፈር ትመልሳላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ የሰው ልጆች

ይህ በአጠቃላይ የሰው ልጆችን መጥቀሻ መንገድ ነው፡፡ "እናንተ የሰው ልጆች" ወይም "እናንተ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ዘንድ ሺህ አመት እንደ ትላንት፣ በምሽት እንዳለፈ አንድ ሰዓት ነው

ጸሐፊው ረጅም ጊዜ ለእግዚአብሔር እንደ አጭር ጊዜ ይቆጠራል ማለቱ ነው፡፡ "አንተ ሺህ አመትን እንዳለፈ አንድ ቀን ወይም በምሽት እንዳለፈ አጭር ጊዜ ትቆጥራለህ" ወይም "ለአንተ ሺህ አመት እንኳን ረጅም ጊዜ አይደለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሺህ አመታት

"1,000 አመታት" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ዐይኖች/እይታ

እዚህ ስፍራ እይታ የሚወክለው አስተያየትን ወይም ምዘናን ነው፡፡ "ለ አንተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)