am_tn/psa/089/046.md

2.7 KiB

ያህዌ ሆይ፣ እስከመቼ ድረስ? ለዘለዓለም ራስህን ትሰውራለህን?

ጸሐፊው እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመባቸው እግዚአብሔርን ንጉሡን አለመቀበሉን እንዲቀጥልበት አለመፈለጉን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ያህዌ ሆይ፣ እባክህ ንጉሡን ለዘለዓለም አትጣለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ራስን ትደብቃለህን

እግዚአብሔር ንጉሡን አለመርዳቱ የተገለጸው እግዚአብሔር ራሱን ከእርሱ እንደሰወረ/እንደ ደበቀ ተደርጎ ነው፡፡ "ንጉሡን አትረዳውምን?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣህ እስከ መቼ እንደ እሳት ይነዳል?

ጸሐፍው ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት እግዚአብሔር እንደ ተቆጣ እንዲቆይ እንደማይፈልግ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "እባከህ ቁጣህ ይብረድ/ ቁጣህ አይቀጥል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣህ እንደ እሳት ይነዳል

እግዚአብሔር በጣም መቆጣቱ የተገለጸው ቁጣዉ የሚነድ እሳት ተደርጎ ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለምን ረብ ለሌለው ነገር የሰው ልጆችን ሁሉ ፈጠርካቸው

"ረብ/ጥቅም የሌለው" የሚለው ረቂቅ ስም "ያለ ጥቅም" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰዎችን ሁሉ ያለ ጥቅም ይሞቱ ዘንድ ፈጠርካቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጆች

ይህ ሰዎችን ሁሉ በጠቅላላ ያመለክታል፡፡ "የሰው ልጆች" ወይም "ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጡንቻማነትን የሚገልጹ ቃላት ሴትን ሲያካትቱ የሚለውን ይመልከቱ)

ላይሞት ነዋሪ የሚሆን ማን ነው፣ ወይም ራሱን ከሲኦል እጅ የሚያድን ማን ነው?

ጸሐፊው እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ሰዎች ሟች እንደሆኑ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ማንም ለዘለዓለም መኖር አይችልም ወይም ማንም ራሱን ከሞት በኋላ ወደ ህይወት መመለስ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)