am_tn/psa/089/044.md

1.1 KiB

ዙፋኑን ወደ ምድር ጣልክ

እዚህ ስፍራ "ዙፋን" የሚወክለው እንደ ንጉሥ የመግዛትን ሀይል ነው፡፡ "አንተ፣ ያህዌ፣ እንደ ንጉሥ ሆኖ የሚገዛበትን ዘመን አበቃህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የወጣትነት ቀናቱን አሳጠርክ

ይህ እግዚአብሔር ንጉሡ ወጣት ሆኖ ሳለ ሽማግሌ እንዲመስል አደረገ ማለት ነው፡፡ "ገና ወጣት ሳለ አንተ እርሱን እንደ ሽማግሌ ሰው ደካማ አደረግኸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእፍረት ሸፈንከው/ከደንከው

ያህዌ ንጉሡን ሙሉ ለሙሉ ማሳፈሩ የተገለጸው፤ እፍረት እግዚአብሔር ንጉሡን ለመሸፈን እንደ ተጠቀመበት ልብስ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)