am_tn/psa/089/041.md

1.9 KiB

ለጎረቤቶቹ

እዚህ ስፍራ "ጎረቤቶች" ማለት በአቅራቢያ አገራት የሚኖሩ ሰዎች ማለት ነው፡፡

የጠላቶቹን ቀኝ እጅ አስነሳሁበት

እዚህ ስፍራ "ቀኝ እጅ" የሚለው የሚወከወለው ሀይልን ነው፡፡ "ቀኝ እጅን ማንሳት" ማለት ያህዌ እርሱ ራሱ የመረጠውን ንጉሥ ጠላቶቹ እንዲያሸንፉት አቅም ሰጣቸው ማለት ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚሉትን ይመልከቱ)

የሰይፉን ስለት አጠፍኩ

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የሚወክለው ንጉሡ በጦርነት ያለውን ሀይል ነው፡፡ ሰይፍን መመለስ/ማጠፍ የሚወክለው ንጉሡን በጦርነት ማሸነፍ እንዳይችል ማድረግን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የሰይፉ ስለት/ጠርዝ

እዚህ ስፍራ "ስለት/ጠርዝ" የሚወክለው ጠቅላላ ሰይፉን ነው፡፡ "የእርሱ ሰይፍ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በጦርነት መሃል መቆም እንዳይችል ማድረግ

እዚህ ስፍራ "መቆም" የሚወክለው በጦርነት ወቅት አሸናፊ መሆንን ነው፡፡ "በጦርነት አሸናፊ እንዲሆን አንተ አልረዳኸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)