am_tn/psa/089/038.md

1.8 KiB

አንተ ተቃወምከው ተውከውም

"ንጉሡ" የሚለው ቃል በውስጠ ታዋቂነት አለ፡፡ "አንተ ንጉሡን ተቃወምከው ወይም ተውከውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለየሚለውን ይመልከቱ)

የቀባኸው ንጉሥ

"አንተ የመረጥከው ንጉሥ"

አንተ ቃል ኪዳኑን ተውክ

"አንተ ቃል ኪዳኑን ጣልክ"

አንተ የእርሱን ዘውድ በመሬት ላይ አረከስክ

ወደ መድር ወይም አፈር ላይ መጣል በታላቅ ሁኔታ ማዋረድን ያመለክታል፡፡ "አንተ የእርሱን ዘውድ ምድር ላይ ጥለህ አቆሸሽክ" ወይም "አንተ የእርሱ ዘውድ ቆሻሻ ላይ እንዲወድቅ አደረግህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ዘውድ

ይህ የሚወክለው እንደ ንጉሥ የንጉሡን ሀይል እና የመግዛት መብት ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ የእርሱን ቅጥሮች ሁሉ አፈረስክ፡፡ ጠንካራ ምሽጎቹን ሁሉ አወደምክ

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ጠላቶች የእየሩሳሌም መከላከያ ሁሉ እንዲወድም መፍቀዱን ነው፡፡ "ጠላቶች የእርሱን ቅጥር እንዲያፈርሱ እና ጠንካራ ምሽጎቹን እንዲደመስሱ ፈቀድክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)