am_tn/psa/089/035.md

2.4 KiB

በቅዱስናዬ ማልኩ

ያህዌ ቅድስናውን ለመሃላው መሰረት አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ ይህ እርሱ ለማድረግ ቃል የገባውን በእርግጥ እንደሚያደርግ የሚያረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡

የእርሱ ዙፋን እንደ ፀሐይ በፊቴ ለዘለዓለም ይሆናል/ይቀጥላል

"ይቀጥላል" የሚለው ቃል በውስጠ ታዋቂነት መኖሩ ይታወቃልለ፡፡ "የእርሱ ዙፋን ፀሐይ በፊቴ እስላለች ድረስ ይቀጥላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለየሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ለዘለዓለም የጸና ይሆናል

እዚህ ስፍራ "ይህ" የሚለው የሚያመለክተው የዳዊትን ዙፋን ወይም እንደ ንጉሥ የመግዛት ሀይሉን ነው፡፡ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ለዘለዓለም የጸና እንዲሆን አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ጨረቃ ለዘለዓለም

እግዚአብሔር የዳዊትን ንጉሣዊ አገዛዝ ከጨረቃ ጋር ያነጻጸረው ከዳዊት ትውልዶች ውስጥ ሁልጊዜም የሚነግስ ሰው እንደሚኖር ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጨረቃይቱ፣ በሰማይ ታማኝ ምስክር

ጨረቃይቱ የተገለጸችው ያህዌ ለዳዊት ቃልኪዳን ሲገባለት ምስክር ሆኖ እንደተገኘ ሰው ተደርጋ ነው፡፡ "ጨረቃይቱ፣ በሰማይ እንደ ታማኝ ምስክር የሆነች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሴላ

ይህ ሰዎች የሙዚቃ መሳሪያቸውን እዚህ እንዴት እንደሚያዜሙበት ወይም እንደሚጫወቱበት የሚያሳይ ሙዚቃዊ ስያሜ ነው፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች የዕብራይስጡን ቃል እንዳለ ይጠቀሙበታል፣ አንዳንድ ትርጉሞች ይተዉታል፡፡ ይህ በመዝሙር 3፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ቅጂ/እንዳለ መገልበጥ/ ወይም ቃላትን መዋስ የሚለውን ይመልከቱ)