am_tn/psa/089/027.md

1.8 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ያህዌ ስለ ዳዊት መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እንደ በኩር ልጄ አድርጌ አስቀምጠዋለሁ

ያህዌ ለዳዊት ልዩ ማዕረግ መስጠቱ እና ኬሌሎች ሰዎች በላይ ለእርሱ ጥበቃ ማድረጉ የተገለጸው፣ ዳዊት የያህዌ የበኩር ልጅ እንደሚሆን ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ ሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ለእርሱ የቃል ኪዳኔን ታማኝነት ለዘለዓለም እቀጥላለሁ

የያህዌ የቃል ኪዳን ታማኝነቱን ለዳዊት እንደሚቀጥል የገለጸው የያህዌ ቃል ኪዳን ታማኝነት እርሱ እንደሚያሰፋው ወይም እንደሚያራዝመው አካል ተደርጎ ነው፡፡ "ታማኝነት" የሚለው ረቂቅ ስም በተውሳከ ግስ መለኩ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔ ለእርሱ ያለኝን ታማኝነት ለዘለዓለም እቀጥላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

የእርሱ ዙፋን በላይ እንደሚገኘው ሰማይ የጸና ነው

ከዳዊት ቤት ንጉሥ እንደማይታጣ የተገለጸው የእርሱ ዙፋን ሰማይ ለዘለዓለም የጸና እንደሆነ ዙፋኑ ለዘለዓለም እንደሚኖር ተደርጎ ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ዙፋን

እዚህ ስፍረ "ዙፋን" የሚወክለው እንደ ንጉሥ የመግዛት ሀይልን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)