am_tn/psa/089/024.md

3.1 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ያህዌ ስለ ዳዊት መናገሩን ቀጥሏል፡፡የእግዚአብሔር የዘላለም ታማኝነት እና ለዳዊት የገባውን እንደሚፈጽምለት የተገለጸው፣ እውነት እና ታማኝነት ከዳዊት ጋር እንደሚሆኙ አካለት ተደርገው ነው፡፡ "እውነት" እና "ታማኝነት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች በቅጽል መልክ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "እኔ ለእርሱ ሁልጊዜም ታማኝ እሆናለሁ ደግሞም ለእርሱ ሁሌም በታማኝነት እፈጽምለታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

በስሜ ድል ይጎናጸፋል

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚለው የሚወክለው የእግዚአብሔርን ሀይል ነው፡፡ "እኔ፣ እግዚአብሔር፣ድል አጎናጽፈዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እጆችን ከባህሮች በላይ፣ ቀኝ እጁንም ከወንዞች በላይ አደርጋለሁ

እዚህ ስፍራ "እጅ" እና "ቀኝ እጅ" የሚሉት የሚወክሉት ሀይልን እና ስልጣንን ነው፡፡ "ባህሩ" ከእስራኤል በስተ ምዕራብ የሜድትራኒያን ባህርን የሚያመለክት ይመስላል፤ "ወንዞች" የሚለው በስተ ምስራቅ የሚገኘውን የኤፍራጥስ ወንዝ ያመለክታል፡፡ ይህ ማለት ዳዊት ከባህሩ እስከ ወንዙ ድረስ ባለው ማናቸውንም ነገር ላይ ስልጣን ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ "እኔ ለእርሱ ከሜድትራኒያን ባህር እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ባለው ማናቸውም ነገር ላይ ስልጣን እሰጠዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ከጽንፍ ጽንፍ /ከዳር ስስከ ዳር/ የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱ፣ ‘አምላኬ ሆይ፣ አንተ አባቴ ፣ የደህንነቴ አለት ነህ' ብሎ ወደ እኔ ይጣራል፡፡

ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዟል፡፡ ቀጥተኛ ባልሆነ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እርሱ እኔን፤ አባቱ፣ አምላኩ፣ እና የደህንነቱ አለት እንደሆንኩ ይናገራል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ እንደዚሁም ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያለሆኑ ጥቅሶች የሚለውን ይመልከቱ)

የደህንነቴ አለት

ያህዌ ዳዊትን መጠበቁ እና ማዳኑ የተገለጸው፤ ያህዌ፣ ዳዊት ከጠላቶቹ ለመዳን በላዩ ሊቆምበት እንደሚችል ከፍ ያለ አለት ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)