am_tn/psa/089/017.md

1.4 KiB

አንተ የእነርሱ ባለ ግርማ ሞገስ ብርታታቸው ነህ

"ብርታት/ጥንካሬ" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እጅግ ብርቱ ታደርጋቸዋልህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ የእነሱ ነህ

እዚህ ስፍራ "የእነሱ" የሚለው የሚያመለክተው እስራኤላውያንን ነው፡፡ ጸሐፊው የእስራኤላውያን አባል አድርጎ አካቷል፡፡ "አንተ የእኛ ነህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ ድል አድራጊ ነን

እዚህ ስፍራ "እኛ" የሚለው የሚያመለክተው ጸሐፊውን እና እስራኤላውያንን ነው፤ ጸሐፊው የሚያናግረውን ያህዌን አይጨምርም፡፡ (የማያካትት እና አካታች "እኛ" የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ የሆነ የእኛ ጋሻ

ህዝቡን የሚጠብቀው እና ያህዌ የመረጠው ንጉሥ የተገለጸው የያህዌ ጋሻ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)