am_tn/psa/089/015.md

1.8 KiB

አንተን የሚያመልኩ

እዚህ ስፍራ "አምልኮ" የሚለው የሚያመለክተው መጮህን እና መለከት/ቀንዶችን መንፋትን ነው፡፡ ይህ በእስራኤላውያን ክብረ በዓል የተለመደ ድርጊት ነበር፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ይሄዳሉ/ይራመዳሉ

እዚህ ስፍራ የሰዎች ኑሮ የተገለጸው እንደሚሄዱ/እንደሚራመዱ ተደርጎ ነው፡፡ "ይኖራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በፊትህ ብርሃን

ጸሐፊው ያህዌ ለእነርሱ ሞገስን እንደሚሰጥ የገለጸው፣ የያህዌ ፊት በእነርሱ ላይ ብርሃንን እንደሚያበራ አድርጎ ነው፡፡ "በእነርሱ ላይ ሞገስህን እንደምታደርግ ይወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በስምህ

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚወክለው ጠቅላላ ሰውነትን ነው፡፡ " በአንተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በጽድቅህ አንተን ከፈ ከፍ ያደርጋሉ

"ጽድቅ" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ ሁልጊዜም ትክክል የሆነውን ስለምታደርግ እነርዱ ከፈ ከፍ ያየርጉሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ "ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)