am_tn/psa/089/013.md

1.9 KiB

አንተ ታላቅ ክንድ እና ጠንካራ እጅ አለህ፣ ደግሞም ቀኝ እጅህ ከፍ ያለ ነው

"ታላቅ ከንድ፣" "ጠንካር እጅ፣" እና "ቀኝ እጅ" የሚሉት ሁሉም የእግዚአብሔርን ሀይል ይወክላሉ፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ቀኝ እጅህ ከፍ ያለ ነው

ቀኝ እጅን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ማንሳት፣ ሀይልን የሚያሳይ ምልክት ፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት)

ጽድቅ እና ፍትህ የዙፋንህ መሰረቶች ናቸው

የእግዚአብሔር በንግሥናው መግዛት እና ትክክልና ተገቢ የሆነውን ማድረግ የተገለጸው፣ የእግዚአብሔር ዙፋን ግንብ እንደሆነ እና ጽድቅና ፍትህ መሰረቶቹ እንደሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዙፋንህ

ዙፋኑ የእግዚአብሔርን እንደ ንጉሥ መግዛት ይወክላል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የቃል ኪዳን ታማኝነት እና ታማኝነት ከፊትህ ይወጣሉ

እግዚአብሔር ሁልጊዜም ታማኝ መሆኑ እና ቃል የገባውን መፈጸሙ የተገለጸው የቃል ኪዳን ታማኝነት እና ታማኝነቱ መጥተው ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚገኛኙ ተደርጎ ነው፡፡ ረቂቅ የሆኑት ስሞች በቅጽል መልክ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "አንተ ሁልጊዜም ለቃል ኪዳንህ ታማኝ ነህ ደግሞም አንተን ላመኑህ ትበጃቸዋለህ" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)