am_tn/psa/089/011.md

1.3 KiB

ሰሜኑ እና ደቡቡ

ጸሐፊው "ሰሜን" እና "ደቡብ" የሚሉትን ቃላት በአንድነት የተጠቀመባቸው፣ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ የሚገኙትን ሁሉንም ነገሮች ፈጥሯል ለማለት ነው፡፡ (ከጽንፍ ጽንፍ የሚለውን ይመልከቱ)

ታቦር እና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይሰኛሉ

ታቦር ከገሊላ በስተ ደቡብ ምዕራብ የሚገኝ ተራራ ሲሆን አርሞንዔም ከገሊላ ባህር በሰሜን ምስራቅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ጸሐፊው እነዚህን ተራሮች የሚገልጸው ደስ መሰኘት እንደሚችሉ ሰዎች አድርጎ ነው፡፡ "ይህ የታቦር ተራራ እና የአርሞንዔም ተራራ በስምህ ደስ እንደተሰኙ ሆኖ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚሉትን ይመልከቱ)

በስምህ

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚወክለው ጠቅላላ ሰውነትን ነው፡፡ " በአንተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)