am_tn/psa/089/007.md

1.1 KiB

እርሱ በቅዱሳኑ ምክርቤት እጅግ የተከበረ አምላክ ነው፡፡

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የቅዱሳኑ ምክርቤት እግዚአብሔርን እጅግ ያከብራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የቅዱሳኑ ምክር ቤት

"የሰማያዊ ፍጥረታት ስብሰባ" ወይም "የመላዕክት ስብሰባ"

ያህዌ ሆይ፣ እንደ አንተ ሀያል ማን ነው?

ጸሐፊው ጥያቄውን ያነሳው እንደ ያህዌ ያለ ሀያል እንደሌለ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ታማኝነትህ ከቦሃል

ያህዌ ሁልጊዜም ለማድረግ ቃል የገባውን ማድረጉ የተገለጸው የእርሱ ታማኝነት ዙሪያውን እንደ ጠቀለለው ልብስ ወይም እንደ ካባው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)