am_tn/psa/089/003.md

2.3 KiB

እኔ ከመረጥኩት ጋር ቃል ሊዳኔን አድርጌያለሁ

"የመረጥኩት " የሚለው ዳዊትን እንደሚያመለክት ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ "እኔ ለመረጥኩተ ለዳዊት ቃል ኪዳን ገብቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ አድርጌያለሁ

ያህዌ በመዝሙር 89፡3-4 ባለው ውስጥ ይናገራል፡፡

እኔ ተውልድህን ለዘለዓለም አጸናለሁ

ያህዌ ሁልጊዜ ከዳዊት ተውልዶች አንዱን እንደሚያነግስ የተገለጸው የዳዊት ትውልዶች የሚያንጸው እና አጠንከሮ የሚያቆመው ህንጻ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በትውልዶች ሁሉ ዙፋንህን አጸናለሁ

እዚህ ስፍራ "ዙፋን" የሚወክለው እንደ ንጉሥ የመምራትን ሀይል ነው፡፡ መዝሙረኛው ከዳዊት ትውልዶች ውስጥ አንዱ ሁልጊዜ ንጉሥ እንደሚሆን እና እንደሚመራ የሚናገረው እግዚአብሔር የዳዊትን ዙፋን እንደሚመሰርት እና እንደሚያጸና አድርጎ ነው፡፡ "ከትውልዶች ውስጥ አንዱ በህዝቤ ላይ በየትውልዱ ንጉሥ ሆኖ እንደሚመራ አረጋግጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ሴላ

ይህ ሰዎች የሙዚቃ መሳሪያቸውን እዚህ እንዴት እንደሚያዜሙበት ወይም እንደሚጫወቱበት የሚያሳይ ሙዚቃዊ ስያሜ ነው፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች የዕብራይስጡን ቃል እንዳለ ይጠቀሙበታል፣ አንዳንድ ትርጉሞች ይተዉታል፡፡ ይህ በመዝሙር 3፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ቅጂ/እንዳለ መገልበጥ/ ወይም ቃላትን መዋስ የሚለውን ይመልከቱ)