am_tn/psa/089/001.md

2.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነግጥም እና ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ማሽል

ይህ የዝማሬ ስልትን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ይህ በመዝሙር 32፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ኤታን

ይህ የጸሐፊው ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ይዝራኤላዊው

ይህ የአንድ ወገን ህዝብ ስያሜ ነው፡፡ ይህ አንድን ወንድ ልጅ ወይም የየዛራን ትውልድ ሊያመለክት ይችላል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የቃል ኪዳን ታማኝነት ድርጊቶች

"ታማኝነት" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ታማኝ ድርጊቶች" ወይም "ተወዳጅ ድርጊቶች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የቃል ኪዳን ታማኝነት ለዘለዓለም ተመስርቷል

እግዚአብሔር ሁሌጊዜም ሊያደርግ ቃል የገባውን ማድረጉ የተገለጸው ታማኝነቱ እርሱ የገነባው እና ያጠነከረው/ያቆመው ህንጻ ተደርጎ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን የተነሳ አንተ ሁልጊዜም ታማኝ ትሆናለህ" (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተ እውነተኛነትህን በሰማያት መሰረትህ

እግዚአብሔር ሁሌጊዜም ሊያደርግ ቃል የገባውን ማድረጉ የተገለጸው ታማኝነቱ እርሱ የገነባው እና ያጠነከረው/ያቆመው ህንጻ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሰማት

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ የእግዚአብሔርን መኖሪያ ስፍራ ያመለክታል፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሔር በሰማይ ሆኖ ይገዛል፣ ደግሞም እርሱ ሁልጊዜም ቃል የገባውን ያደርጋል፤ ወይም 2) ይህ ሰማይን ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንደ ሰማይ የጸና እና ቋሚ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)