am_tn/psa/087/005.md

2.2 KiB

የጽዮን የሆኑ ይባላል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰዎች ስለ ጽዮን ይናገራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ እያንዳንዳቸው የተወለዱት በዚህ ነበር

ያህዌን የሚያመልኩ ከሌሎች አገራት የመጡ ሰዎች በእየሩሳሌም እንደ ተወለዱ ተደርጎ ይነገራል፡፡ "ይህም እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእየሩሳሌም እንደተወለዱ ይቆጠራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በ እርሷ

ከተሞችን "እርሷ" ብሎ መጥራት የተለመደ ነበር፡፡ "በእየሩሳሌም" ወይም "በጽዮን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ከሁሉም ከፍ ያለው /ልዑሉ ራሱ

ጸሐፊው "እርሱ ራሱ" የሚለውን ደጋጋሚ ተውላጠ ስም የተጠቀመው ይህንን ያደረገው ልዑሉ ራሱ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ደጋጋሚ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እርሷን ያጸናታል

"እየሩሳሌምን ጠንካራ ያደርጋታል"

ያህዌ በአገራት የህዝብ ቆጠራ መጽሐፍ ላይ ሲጽፍ

ያህዌ የሌላ አገር ሰዎችም የእርሱ እንደሆኑ እውቅና መስጠቱ የተገለጸው፣ በእርሱ ከተማ የሚኖሩ ሰዎችን ስሞች እንደጻፈ ንጉሥ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህኛው የተወለደው እዚህ ነበር

"ይህኛው" የሚለው የሚያመለክተው ጸሐፊው ከጠቀሳቸው አገራት የሆኑ ሰዎችን ነው፡፡ ምንም እንኳን በአካል በጽዮን ባይወለዱም፣ እግዚአብሔርን የሚከተሉ/የሚያመልኩ በመንፈስ የእየሩሳሌም ተወላጆች ናቸው፡፡ ይህ በመዝሙር 87፡4 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)