am_tn/psa/087/001.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነግጥም እና ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

የቆሬ ልጆች ዝማሬ፣ ዝማሬ

"ይህ የቆሬ ልጆች የጻፉት ዝማሬ ነው"

የጽዮን በሮች

እዚህ ስፍራ "የጽዮን በሮች" የሚለው የሚወክለው መላዋን የእየሩሳሌም ከተማ ነው፡፡ "የኢየሩሳሌም ከተማ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

መላው የያዕቆብ ድንኳኖች

በበረሃ በሚንከራተቱበት ወቅት በድንኳኖች የኖሩ ሰዎች፡፡ እዚህ ስፍራ ጸሐፊው "የያዕቆብ ድንኳኖች" የሚለውን የተጠቀመበት እስራኤላውያን አሁን የሚኖሩነትን ለመግለጽ ነው፡፡ "ማናቸውም አሁን እስራኤላውያን የሚገኙባቸው ሌሎች የመኖሪያ ስፍራዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ ነገሮች ተነግረዋል

ጸሐፊው ለእየሩሳሌም ከተማ እርሱን እንደምትሰማው አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እናንተ በእየሩሳሌም የምትኖሩ ሰዎች ሆይ፣ ሌሎች ሰዎች ስለ እናንተ ከተማ አስደናቂ ነገሮችን ይናገራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አጋኖ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ሴላ

ይህ ሰዎች የሙዚቃ መሳሪያቸውን እዚህ እንዴት እንደሚያዜሙበት ወይም እንደሚጫወቱበት የሚያሳይ ሙዚቃዊ ስያሜ ነው፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች የዕብራይስጡን ቃል እንዳለ ይጠቀሙበታል፣ አንዳንድ ትርጉሞች ይተዉታል፡፡ ይህ በመዝሙር 3፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ቅጂ/እንዳለ መገልበጥ/ ወይም ቃላትን መዋስ የሚለውን ይመልከቱ)