am_tn/psa/085/003.md

1.7 KiB

ቁጣህን ሁሉ አስቀረህ

ከእንግዲህ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ቁጣው እንደማይቀጥል የተገለጸው፣ ቁጣ እሳት እንደሆነ እናእግዚአብሔር ከዚያ ፊቱን እንደመለ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የደህንነታችን አምላክ

"ደህንነት" የሚለው ረቂቅ ስም በግሥ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ያዳነን እግዚአብሔር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በእኛ ደስ አለመሰኘትህ ያብቃ

እግዚአብሔር በእስራኤላውያን መቆጣቱ እንዲያበቃ መለመኑ የተገለጸው፣ ጸሐፊው ደስ አለመሰኘትን እግዚአብሔር እንዲወስደው የሚፈልገው ቁስ አካል እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ በእኛ ላይ ለዘለዓለም ትቆጣለህን? ቁጣህ በሚቀጥለውም ትውለድ ዘመን ውስጥ ሁሉ ይቀጥላልን?

ጸሐፊው እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ መቆጣቱ እንዲያበቃ እየለመነ መሆኑን ለማጉላት ነው፡፡ እነዚህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "እባክህ በእኛ ላይ ለዘለዓለም አትቆጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)