am_tn/psa/084/011.md

1.4 KiB

ያህዌ አምላክ ፀሐያችን እና ጋሻችን ነው

ህዝቡን የሚጠብቀው እና የሚመራው ያህዌ የተገለጸው ፀሐይ እና ጋሻ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "ያህዌ አምላክ ከፀሐይ እንደሚወጣ ብርሃን ይመራናል፣ ደግሞም እንደ ጋሻ ሆኖ ይጠብቀናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ ጸጋ እና ክብር ይሰጣል

"ጸጋ" እና "ክብር" የሚሉት ረቂቅ ስሞች በግሥ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "ያህዌ ለእኛ መልካም ይሆንልናል ደግሞም ያከብረናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በቅንነት የሚራመድ

አንድ ሰው ህይወቱን የሚመራበት መንገድ ወይም ድርጊቱ የተገለጸው ያ ሰው እንደሚራመድ ተደርጎ ነው፡፡ "በሀቀኝነት የሚኖር" ወይም "ሀቀኛ የሆኑ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የተባረከ ሰው ነው

እዚህ ስፍራ "ሰው" የሚያመለክተው በአጠቃላይ ሰዎችን ነው፡፡ (የስማዊ ሀረግ ክፍል እና ወንዴ መጠሪያ/ቃላት ሴቶችን ሲያካለትት የሚለውን መልከቱ)