am_tn/psa/084/007.md

2.1 KiB

ከሀይል ወደ ሀይል ይሄዳሉ

ይህ እየበረቱ ይሄዳሉ የሚለው የሚገለጽበት መንገድ ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይሄዳሉ

እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ለማምለክ ወደ ቤተመቅደስ ለመሄድ ብርቱ ፍላጎት ያላቸውን ነው፡፡

ሴላ

ይህ ሰዎች የሙዚቃ መሳሪያቸውን እዚህ እንዴት እንደሚያዜሙበት ወይም እንደሚጫወቱበት የሚያሳይ ሙዚቃዊ ስያሜ ነው፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች የዕብራይስጡን ቃል እንዳለ ይጠቀሙበታል፣ አንዳንድ ትርጉሞች ይተዉታል፡፡ ይህ በመዝሙር 3፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ቅጂ/እንዳለ መገልበጥ/ ወይም ቃላትን መዋስ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር፣ ከጋሻችን በላይ ይመለከታል

ህዝቡን የሚጠብቀው ንጉሥ የተገለጸው ጋሻ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር ከንጉሣችን በላይ ይመለከታል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ አደባባዮች ለአንድ ቀን መሆንበሌላ ስፍራ ሺህ ቀን ከመኖር ይሻላል

ይህ በሚታወቅ መረጃ ሊገጽ ይችላል፡፡ "በሌላ ስፍራ ለሺህ ቀናት ከመሆን በአንተ አደባባዮች ለአንድ ቀን መሆን ይሻለኛል" (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሺህ

"1,000" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ዘብ ጠባቂ መሆን

"በበር ላይ ጠባቂ መሆን" ወይም "በር ላይ መቆም"

ክፉዎች

ይህ ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ክፉ ሰዎች" ወይም "ክፉ የሆኑ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)