am_tn/psa/084/005.md

2.2 KiB

የተባረከ ሰው ነው

እዚህ ስፍራ "ሰው" የሚያመለክተው በአጠቃላይ ሰዎችን ነው፡፡ (የስማዊ ሀረግ ክፍል እና ወንዴ መጠሪያ/ቃላት ሴቶችን ሲያካለትት የሚለውን መልከቱ)

አንተ ብርታታቸው የሆንክ

ስለ እግዚአብሔር የተነገረው ሀይል በእርሱ እንደሚገኝ ተደርጎ ነው፡፡ "አንተ ያበረታሃቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የጽዮን መንገዶች በማን ልብ ይገኛል

ይህ አገላለጽ ልባዊ ምኞትን ያመለክታል፡፡ "እስከ ጽዮን መድረስ የሚወዱ" ወይም "በእውነት እስከ ጽዮን መድረስ የሚፈልጉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጎዳና

በዙሪያው ከሚገኘው መሬት ከፍ ብለው የተገነቡ መንገዶች

እስከ ጽዮን ድረስ

ቤተመቅደሱ የሚገኘው ጽዮን ተብሎ በሚጠራው በእየሩሳሌም በሚገኘው ከሁሉም ከፍ ባለው ኮረብታ ላይ ነበር

የእንባ ሸለቆ

ይህ የሚያመለክተው ደረቅ እና የማይታረስ ስፍራን ነው፡፡ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅጂዎች "የባካ ሸለቆ" የሚል ይጨምራሉ፡፡ "ባካ" ማለት "ለቅሶ" ማለት ነው፡፡

የመጀመሪያ/ቀዳሚ ዝናብ

ይህ ማለት ከክረምቱ አስቀድሞ በበልግ የሚዘንበው ዝናብ ማለት ነው፡፡ ይህም በምዕራባውያን የወር አቆጣጠር በጥቅምት እና ህዳር ወራት ማለት ነው፡፡

በረከቶች

እዚህ ስፍራ "በረከቶች" የሚለው ቃል በደረቅ ምድር የሚኖሩ ሰዎችን ደስተኛ ለሚያደርግ የኩሬ ውሃ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እነርሱን ደስ የሚያሰኝ የኩሬ ውሃ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (rc://*/ta/vo12/translate/figs-metonomy) ይመልከቱ፡፡