am_tn/psa/084/001.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነግጥም እና ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ለመዘምራን አለቃ

"ይህ ለመዘምራን መሪ በአምልኮ ጊዜ የሚውል ነው"

ጊተት በሚባል (ዋሽንተ መሰል) የሙዚቃ መሳሪያ የሚቀርብ

ይህ ምናልባት የሙዚቃን/ዝማሬን አይነት ያመለክት ይሆናል፡፡ በመዝሙር 8፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

የቆሬ ልጆች መዝሙር

"ይህ የቆሬ ልጆች የጻፏቸው መዝሙሮች ናቸው"

እንዴት የተወደደ

"እንዴት ውብ"

የያህዌን አደባባይ እጠብቃለሁ

"በያህዌ አደባባይ መሆን እፈልጋለሁ"

የያህዌ አደባባይ

እዚህ ስፍራ "አደባባይ" የሚወክለው ቤተ መቅደስን ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ለዚህ ያለኝ ጥበቃ አጓጉቶኛል

"በጉጉት ዝያለሁ" ወይም "ይህን እጅግ ከመፈለጌ የተነሳ ደክሜያለሁ"

ልቤ እና ጠቅላላው ማንነቴ ይጣራሉ

እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚወክለው ጠቅላላ ስብዕናን ነው፡፡ "በመላው ማንነቴ ፈለግሁ" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ህያው አምላክ

ይህ ማለት እግዚአብሔር ህያው ነው፣ ደግሞም እርሱ ሌሎች ነገሮች ሁሉ አንዲኖሩ የማድረግ ሀይል አለው፡፡