am_tn/psa/082/001.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው

የአሳፍ መዝሙር

"ይህ አሳፍ የጻፈው ዝማሬ ነው"

መለኮታዊ ጉባኤ

"ሰማያዊው ምክር ቤት" ወይም "በሰማይ የተደረገ ስብሰባ"

እርሱ ፍርድ አደረገ

"እርሱ ፍርድ ሰጠ፡፡" "ፍርድ" የሚለው ረቂቅ ስም በግስ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እርሱ ፈረደ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አማልዕክት

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እነዚህ በሰማይ የሚኖሩ ሌሎች መንፈሳዊ አካላት ናቸው፡፡ "መለኮታዊ አካላት" ወይም "ሰማያዊ ፈራጆች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፤ ወይም 2) እነዚህ እግዚአብሔር ለዳኝነት የሾማቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በማንኛውም መንገድ ቢሆን፣ ያህዌ እምላክ እንደሆነው ያሉ አማልዕክት ናቸው ማለት አይደለም፡፡ የዚህ ትርጉም እግዚአብሔር ታላቅ ስልጣን እና ሀይል ሰጥቷቸዋል ማለት ነው፡፡ "መሪዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እስከ መቼ ያለ ቅንነት ትፈርዳላችሁ፣ እስከ መቼስ ለክፉዎች ታደላላችሁ?

ያህዌ ጥያቄውን የተጠቀመበት ዳኞች ለህዝቡ በቅንነት ባለመፍረዳቸው ለመውቀስ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ሴላ

ይህ ሰዎች የሙዚቃ መሳሪያቸውን እዚህ እንዴት እንደሚያዜሙበት ወይም እንደሚጫወቱበት የሚያሳይ ሙዚቃዊ ስያሜ ነው፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች የዕብራይስጡን ቃል እንዳለ ይጠቀሙበታል፣ አንዳንድ ትርጉሞች ይተዉታል፡፡ ይህ በመዝሙር 3፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ቅጂ/እንዳለ መገልበጥ/ ወይም ቃላትን መዋስ የሚለውን ይመልከቱ)