am_tn/psa/081/006.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር መናገር ይጀምራል፡፡

ከጫንቃው ሸክሙን አስወገደ

እዚህ ስፍራ "ከጫንቃው ሸክሙን" የሚለው የሚወክለው አስራኤላውያን በግብጽ ውስጥ በባርነት በነበሩበት ጊዜ ይሰሩት የነበረውን የግዴታ ስራ ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እጆቹ ቅርጫት ከመሸከም ነጻ ወጡ

እዚህ ስፍራ "ቅርጫት መሸከም" የሚለው የሚወክለው አስራኤላውያን በግብጽ ውስጥ በባርነት በነበሩበት ጊዜ ይሰሩት የነበረውን የግዴታ ስራ ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በጭንቀትህ

"በታላቁ መከራህ"

በጨለማና ነጎድጓዳማ ደመና ውስጥ ለጥያቄህ መልስ ሰጠሁህ

እግዚአብሔር ወደ እስራኤላውያን ሲመጣ፣ ሙሉ መገኘቱን እና ክብሩን፣ በጨለማ እና አስፈሪ ደመና ውስጥ ይሰውራል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በመሪባ ውኾች ፈተንኩህ

እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች በመሪባ በረሃ ውሃ እንደሚሰጣቸው ያምኑ እንደሆነ ለማየት ፈተናቸው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)