am_tn/psa/079/012.md

2.1 KiB

ጌታ ሆይ፤… የተዘባበቱበት መዘባበት… አንተ መልስላቸው

አሳፍ የጎረቤት አገሮች በእስራኤል ላይ የሰሩት ክፉ ስራ እንደ “መዘባበት” እንደሆነና እነዚህ ስድቦች እንደ ቁሳቁሶች እንደሆኑ አድርጎ ተናግሯል፡፡ እነዚህን ድርጊቶች እንዲቆጥርባቸው ጌታን ይጠይቃል፣ የጎረቤት አገሮች ስላደረጉት ሰለ እያንዳንዱ ድርጊት በእነዚህ የጎረቤት አገሮች ላይ ሌላ አካል አስነስቶ ሰባት እጥፍ ክፉ ስራ በእነርሱ ላይ እዲያደርግባቸው ጌታን ይጠይቃል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፈላቸው

“መልስላቸው” ወይም “መልሰህ ስጣቸው”

በጭናቸው ላይ

በተቀመጡበት በጉልበታቸውና በታፋቸው፡፡ ይህ “በቀጥታና በግለሰብ ደረጃ” ለመፈፀሙ ተለዋጭ ቀይቤ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ ህዝብህ፣ የማሰማሪያ በጎችህ፣ ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሀለን

“በጎች” የሚለው ቃል እረኛ ለሚጠብቃቸውና ለሚመራቸው ረዳት አልባ ሰዎች ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ የምትጠብቀንና የምትመራን እኛ ህዝብህ ለዘላለም እናመሰግንሀለን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምስጋናህን ለትውልድ ሁሉ እንናገራለን

“የሚመጣው ትውልድ በሙሉ የሰራኸውን መልካም ነገሮች በሙሉ እንዲያውቁ በእርግጠኝነት እናደርጋለን”

ምስጋናህን

ይህ ሰዎች ጌታን የሚያመሰግኑባቸው እርሱ የሰራቸው ነገሮችን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ስለ ሰራሀቸው ነገሮች አንተን ማመስገን እንዲቀጥሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)