am_tn/psa/079/006.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እነዚህ ሁለት ጥንድ ሀረጎች እያንዳንዳቸው ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በአንድ ላይ የተጣመሩት አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

በህዝቦች ላይ መአትህን አፍስስ

አሳፍ ስለ እግዚአብሔር መአት ሲናገር ፈሳሽ እንደሆነ አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ስለተቆጣህ ህዝቦችን ቅጣቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ስምህን በማይጠሩ

“ስም” የሚለው ቃል ለሰውየው ሀይልና ስልጣን ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአንተ ያልሆኑት ወይም እንድትረዳቸው ለማይጠይቁህ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ያዕቆብን በልተውታልና

“ያዕቆብ” የሚለው ቃል ልጆቹ ለሆኑት ለእስራኤል ህዝብ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤልን ህዝብ ሙሉ በሙሉ አጠፏቸው” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)