am_tn/psa/079/004.md

1.7 KiB

እኛም ለጎረቤቶቻችን መዘባበቻ፤ በዙሪያችንም ላሉት መሳቂያና መሳለቂያ ሆንን

“መዘባበቻ እና መሳቂያ የሚሉት ቃላቶች ሌሎች ለሚዘባበቱባቸው፣ ለሚስቁባቸውና ለሚሳለቁባቸው ምትክ ስሞች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ ጎረቤቶቻቸው የሚስቁባቸውን የሚሳለቁቸው ሰዎች ሆነናል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ሆነናል

“እኛ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ህዝብ ነው፡፡

መሳለቂያ

አንድን ሰው ለማዋረድ የሚደረግ ብርቱ ሳቅ ነው፡፡

የቅናትህ ቁጣ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?

ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “የቅናት ቁጣህ እንደ እሳት መንደዱን ፈፅሞ የሚቆም አይመስልም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የቅናትህ ቁጣ ይነድዳልን

“ቁጣ” የሚለው ረቂቅ ስም ቁጡ ተብሎ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቀናተኛና ቁጡ ትሆናለህን” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ እሳት ይነድዳል

ይህ ተነፃፃሪ ዘይቤ የእግዚአብሔር ቁጣ መገለጠ ነገሮች ከሚያጠፋ እሳት ጋር ያነፃፅረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አጠፋን” (ተነጻጻሪ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)