am_tn/psa/078/067.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጸሐፊው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰራውን ስራ መግልጽ ቀጥሏል።

የዮሴፍ ድንኳን

እዚህ ላይ “ድንኳን” የሚለው ቃል ለቤተሰብ ምትክ ስም ነው፡፡ በዚህ ሀረግ ድንኳን የዮሴፍን ልጆች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የዮሴፍ ልጆች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ዮሴፍ… ኤፍሬም

ኤፍሬም የዮሴፍ ልጅ ነበር፡፡

ይሁዳ… የፅዮን ተራራ

የጽዮን ተራራ የሚገኘው የይሁዳ ነገድ ይኖርበት በነበረው ምድር ነው፡፡

መቅደሱን እንደ ሰማያት ሰራት

የዚህ ንፅፅር ዘይቤ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፡- 1) እግዚአብሔር መቅደሱን እንደ ሰማያት ከፍ አድርጎ ሰራት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መቅደሱን አንደ ሰማያት ከፍ አድርጎ ሰራት” ወይም 2) እግዚአብሔር መቅደሱን እንደ ሰማያት የማይናወጥ አድርጎ ሰራት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰማያት ለዘላለም ፀንተው እንደሚኖሩ እንደዚሁ መቅደሱን ለዘላለም ፀንታ እንድቅቆም አድርጎ ሰራት” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ምድር

ይህ ግስ የተሰጠው ከቀደመው መስመር ሊሆን ይችላል፡፡ ጸሐፊው የእግዚአብሔርን መቅደስ ቋሚነት ከምድር ቋሚነት ጋር አነፃፅሮታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድር በቋሚነት እንደሚኖር እንዲሁ እርሱ መቅደሱን በቋሚነት እንዲኖር አድጎ ሰራት፡፡” (አስጨምሬ እና ተንጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)