am_tn/psa/078/064.md

2.0 KiB

ካህናቶቻቸው በሰይፍ ወደቁ

እዚህ ላይ “ሰይፍ” የሚለው ቃል በሰይፍ የሚዋጉ ወታደሮችን የሚወክል ነው፡፡ “በሰይፍ ወደቁ” የሚለው ሀረግ ፈሊጥ ሲሆን በጦርነት መካከል መሞት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ካህናቶቻቸው በጦርነት መካከል ሞቱ” ወይም “ጠላት ካህናቶቻቸውን በሰይፍ ገደላቸው” (ምትክ ስም እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

መበለቶቻቸው ማልቀስ ተሳናቸው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) አንድ ሰው መበለቶች እንዳያለቅሱ አስገደዳቸው ወይም 2) ብዙ ካህናቶች ከመሞታቸው የተነሳ አግባብነት ያለው የቀብር ስርአት ለመፈፀም ጊዜ አልነበረም፡፡

መበለቶች

ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች

ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሳ

ጌታ ለተወሰነ ጊዜ ስራ ስለ አለመስራቱ ሲናገር እርሱ ተኝቶ እንደነበረ ተደርጎ ሲገለፅ፣ ስራ መጀመሩ ደግሞ ከእንቅልፍ መነሳቱ ተደርጎ ተገልጧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደነቃ ያህል ስራ መስራት ጀመረ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የወይን ጠጅ ስካር እንደ በረደለት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) ብዙ የወይን ጠጅ እንደጠጣና እንደሰከረ ከስካሩም በመንቃቱ ምክንያት ለመዋጋት እንደፈለገ በቁጣም እንደተሞላ ተዋጊ ወይም 2) ብዙ የወይን ጠጅ እንደጠጣ ነገር ግን አሁን ማሰብ እንደቻለና ከመተኛቱ የተነሳ በሚገባ እንደተዋጋ ተዋጊ፡፡