am_tn/psa/078/062.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጸሐፊው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰራውን ስራ መግልጽ ቀጥሏል።

ህዝቡን ለሰይፍ አሳልፎ ሰጠ

አሳፍ ስለ እግዚአብሔር ህዝብ ሲናገር እግዚአብሔር እንደ ስጦታ ለሌሎች የሚሰጣቸው ትንሽ እቃ እንደሆኑ፣ በጦርነት ለሚከሰት ሞት ምትክ ስም የሆነውን ሰይፍ ደግሞ ስጦታውን ሊቀበል የሚችል ሰው እንደሆነ አደርጎ ገልጧቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ሌሎች ሰዎች ህዝቡን በጦርነት ውስጥ እንዲገድሏቸው ፈቀደ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ሰውኛ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በርስቱ ላይ እጅግ ተቆጣ

“ለዘላለም የራሱ ይሆናል ብሎ የተናገረላቸው ህዝቡ ላይ ተቆጣ”

ጎልማሶቻቸውን እሳት በላቸው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) “ጎልማሶቻቸውን በሙሉ ለመግደል ጠላት እሳት ተጠቀመ” ወይም 2) “ጎልማሶቻቸው በጦርነት ውስጥ እሳት ደረቅ ሳርን እንደሚያቃጥል እንደዚሁ በፍጥነት ሞቱ፡፡” እነዚህ ሰዎች የጦር መሳሪያ እንደተጠቀሙ የሚያሳይ መልእክት አታስተላልፍ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በላቸው

“መብላት” ማንኛውንም ነገር በጣም በፍጥነት መብላት ነው፡፡

ሰርግ

ሰዎች ሲያገቡ የሚፈፀም ስርአት