am_tn/psa/078/060.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጸሐፊው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰራውን ስራ መግልጽ ቀጥሏል።

የሀይሉን ምልክት አስማረካት፤ ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ

አሳፍ ስለ እግዚአብሔር ሀይልና ክብር ሲናገር እነዚህ ሁለቱ ሰዎች ሊይዟቸውና ሊሸከሟቸው የሚችሉ ቁሳዊ እቃዎች እንደሆኑ አድርጎ ገልጧቸዋል፡፡ “ሀይል” እና “ክብር” የሚሉት ቃላቶች ምናልባት ለቃል ኪዳኑ ታቦት ምትክ ስሞች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ “እጅ” የሚለው ቃል ለጠላት ሀይል ምትክ ስም ነው፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቹ የከበረውን የቃል ኪዳኑን ታቦት እንዲማርኩት ፈቀደ፤ ታቦቱን የፈለጉትን ማንኛውንም ነገር ሊያደርጉበት እንዲችሉ ለእነርሱ አሳልፎ ሰጣቸው” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)