am_tn/psa/078/056.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጸሐፊው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰራውን ስራ መግልጽ ቀጥሏል።

ተፈታተኑት፣ አመፁ

እነዚህ ቃላቶች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ጸሐፊው እነዚህን የተጠቀመው እግዚአብሔር ለእነርሱ የሚያስፈልጋቸውን እንደሚያዘጋጅላቸው ወይም እንደተናገረው ክፉውን እንደሚቀጣ እስራኤላውያን ፈፅመው እንደማያምኑ አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ተፈታተኑት

እግዚአብሔር አደርገዋለሁ ብሎ የተናገረውን ነገር ማድረግ እንደሚችል እርሱን ከማመናቸው በፊት እንዲያረጋግጥላቸው ፈለጉ፡፡ ይህን በ መዝሙረ ዳዊት 78:18 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

አመጹ

ለመታዘዝ እንቢ አሉ

ከዳተኞች ነበሩ፣ ክፋትንም አደረጉ

እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ጸሐፊው ሁለቱንም ሀረጎች የተጠቀመባቸው እስራኤላውያን እናደርጋለን ብለው የተናገሩትን ነገር ለእግዚአብሔር እንዳላደረጉ አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)