am_tn/psa/078/054.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጸሐፊው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰራውን ስራ መግልጽ ቀጥሏል።

ቀኝ እጁ አባረረ

“ቀኝ እጅ” የሚሉት ቃላቶች ለሀይል ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ በራሱ ሀይል ለራሱ አሸነፈ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ርስታቸውን አከፋፈላቸው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በአንድ ወቅት ሌሎች ህዝቦች ይኖሩበት በነበረው ምድር ርስታቸውን አከፋፈላቸው ወይም 2) እግዚአብሔር በአንድ ወቅት ከርስታቸው ወደ ሌላ አውጥቶ ለሰደዳቸው አህዛብ ርስታቸውን አካፈላቸው፡፡ “ሁልጊዜ ለእነርሱ የሚሆን ምድር ሰጣቸው”

በድንኳናቸው ውስጥ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) እርሱ እስራኤላውያንን በምድሪቱ በራሳቸው ድንኳኖች አኖራቸው ወይም 2) እርሱ እስራኤላውያንን ሌሎች ህዝቦችን አባርሮ ባወጣበት ድንኳኖች አኖራቸው፡፡ እነዚህ “ድንኳኖች” አብዛኛዎቹ እውነተኛ ቤቶች ነበሩ፣ እነዚህ ቤቶች ደግሞ ሌሎች ህዝቦች በውስጣቸው የኖሩባቸውና እስራኤላውያኑ ራሳቸው የኖሩባቸው ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በራሳቸው ቤት” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)