am_tn/psa/078/047.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጸሐፊው እግዚአብሔር ለግብጻውያን የሰራውን ስራ መግልጽ ቀጥሏል።

ወይን

ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ

የመብረቅ እሳት

ትልቅ ነጎድጓድ የሚያስከትል መብረቅ

እርሱ በረዶ አዘነበባቸው

“እርሱ በረዶ አወረደ” ወይም “በረዶ እንዲወርድ አደረገ”

ፅኑ ቁጣውን በእነርሱ ላይ ሰደደ

አሳፍ ስለ እግዚአብሔር መቅሰፍት ሲናገር መቅሰፍቱ ሌላ ሰውን እንደሚያጠቃ ሰው እንደሆነ አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ በእነርሱ ላይ ተቆጣ፣ ከዚህ የተነሳ በድንገት በመአቱ አጠቃቸው” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ፅኑ ቁጣ

“የእርሱ ፅኑ ቁጣ”

በእነርሱ ላይ ሰደደ

“በእነርሱ ላይ አንድም ነገር ይሆናል ብለው ሳያስቡት አጠቃቸው”

መከራ እንደሚያመጡ ወኪሎች ቁጣ፣ መአትና መቅሰፍት ላከባቸው

አሳፍ ስለ ቁጣ፣ መአትና መቅሰፍት ሲናገር እግዚአብሔር ስራውን ለእርሱ ለመስራት ሊልካቸው እንደሚችላቸው ሰዎች አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ በጣም ከመቆጣቱ የተነሳ ግብፃውያንን መጉዳት ፈለገ፣ ከዚህ የተነሳ በእነርሱ ላይ መከራ ላከባቸው፣ መቅሰፍት ደግሞ አመጣባቸው” (ሰውኛ ዘይቤ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መአት

አንድ ሰው ሌሎችን ለመጉዳት የሚያነሳሳ ቁጣ