am_tn/psa/078/044.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጸሐፊው እግዚአብሔር የሰራውን ስራ ይገልጻል።

የዝንብ ሰራዊት

እንደ ደመና የሚመስል እጅግ ብዙ ዝንቦች፡፡

እነርሱን ነደፏቸው

ዝንቦቹ ግብፃውያንን ቢበሏቸው ኖሮ ሊሰማቸው ይችል እንደነበር እንደዚሁ ግብፃውያንን እንዲያዝኑ አድርገዋቸዋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ እና ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አዝመራቸውን ለኩብኩባ፣ ሰብላቸውን ለአንበጣ ሰጠባቸው

“ኩብኩባ አዝመራቸውን በሙሉ እንዲበሉ አንበጣ ደግሞ ለማምረት ሲሉ እጅግ በጣም ደክመው የሰሩትን ማንኛውንም ነገር እንዲበሉ ፈቀደላቸው”

ምድራቸውን ወረሩት

“በምድራቸው በየትኛውም አቅጣጫ ሄዱ”

ኩብኩባ

ለመዝለል የሚረዱ ረጃጅም እግሮች ያሉት ዕፅዋት የሚበላ ነፍሳት

አዝመራቸውን ለኩብኩባ ሰጠ

አሳፍ ስለ አዝመራው ሲናገር እግዚአብሔር ለኩብኩባው የሰጠው ስጦታ እንደሆነ አደርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አዝመራቸውን እንዲበላባቸው እርሱ ለኩብኩባው ፈቀደለት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የደከሙበትን ሁሉ ለአንበጣ ሰጠ

“እርሱ የደከሙበትን ማንኛውም ነገር ለአንበጣ ሰጠ፡፡” አሳፍ ሰዎቹ የደከሙበትን ነገር እግዚአብሔር ለአንበጣዎች የሰጠው ስጦታ እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡” “የደከሙበት ነገር” የሚለው ሀረግ በድካማቸው ለማምረት በተዘጋጀው እህል ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እጅግ በጣም ደክመው ለምርት የበቃውን እህል አንበጣዎች እንዲበሉት ፈቀደላቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)