am_tn/psa/078/035.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እስራኤላውያን ስለ ሰሯቸው ስራዎች የሚናገሩ ንግርቶች፡፡

አስብ

“አስታውስ፡፡” ይህ በ መዝሙረ ዳዊት 20:3 ላይ እንዴት እደተተረጎመ ተመልከት፡፡

እግዚአብሔር አለታቸው ነበር

ጸሀፊው ስለ እግዚአብሔር ሲናገር እርሱ ሰዎች ከጠላቶቻቸው እንዲድኑ ሄደው የሚጠጉበት ኮረብታ ወይም ተራራ እንደሆነ አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ የሚጠብቃቸው እግዚአብሔር ነበር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አዳኛቸው

“እነርሱን የሚያድናቸው”

ሸነገሉት

“በልባቸው ሳያምኑበት እርሱ አስደናቂ አምላክ እንደሆነ ነገሩት”

በአፋቸው

“አፍ” የሚለው ቃል አፋቸውን በመጠቀም እነርሱ ለሚናገሯቸው ቃላቶች ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተናገሩትን በመናገር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ልባቸው በእርሱ የፀና አልነበረም

እዚህ ላይ ”ልባቸው” ለሀሳባቸው ምትክ ስም ነው፡፡ ለእርሱ ታማኝ መሆን ከእርሱ ጋር በአፅንኦት መጠበቅ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሀሳባቸው በእርሱ ላይ ያተኮረ አልነበረም” ወይም “ለእርሱ ታማኞች አልነበሩም” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)