am_tn/psa/078/033.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ጸሐፊው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰራውን ስራ መናገሩን ቀጥሏል።

ቀኖቻቸውን አሳጠረው

እዚህ ላይ “ቀኖች” የሚለው ቃል የህይወት ዘመናቸውን ያመለክታል፡፡ “ቀኖቻቸውን አሳጠረ” የሚለው ፈሊጥ ረጅም ዘመን ከመኖራቸው በፊት እንዲሞቱ አደረጋቸው የሚል ትርጉም አለው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ገና ወጣቶች ሳሉ ገደላቸው” (ለስላሴ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አመቶቻቸው በድንጋጤ የተሞሉ ነበሩ

አሳፍ ስለ “አመቶች” ሲናገር ማጠራቀሚያ እንደሆኑ አድርጎ ገልጧቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከአመት ወደ አመት ሁልጊዜ በፍርሀት ይኖሩ ነበር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ለመፈለግ

ይጠብቃቸው ዘንድ ሊያደርግላቸው የሚፈልጉትን ነገር ለመጠየቅ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)