am_tn/psa/078/023.md

1.8 KiB

እርሱ ሰማያትን አዘዘ

አሳፍ ስለ ሰማያት ሲናገር ሊሰማ የሚችልና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚያደርግ ሰው እንደሆነ አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ለሰማይ ተናገረ” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰማያት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) “ሰማይ” ወይም 2) “ደመናት፡፡”

የሰማይንም ደጆች ከፈተ

አሳፍ ስለ ሰማይ ሲናገር በር ያለው መጋዘን እንደሆነ አድርጎ አቅርቦታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰማይን እንደ መጋዘን ከፈተው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይበሉም ዘንድ መና አዘነበላቸው፤ ከሰማይም መብልን ሰጣቸው

እነዚህ ሁለት መስመሮች ስለ ተመሳሳይ ክስተት ያወራሉ፡፡

መና አዘነበላቸው

“መና ከሰማይ እንደ ዝናብ እንዲፈስስላቸው አደረገ”

የመላዕክት እንጀራ

ይህ እግዚአብሔር ለህዝቡ የሰጠውን መና የሚያመለክት ነው፡፡ “እንጀራ” የሚለው ቃል በአጠቃላይ ምግብን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መላዕክት የሚበሉት አይነት ተመሳሳይ ምግብ” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

የተትረፈረፈ ምግብ

“የተትረፈረፈ” የሚለው ረቂቅ ስም በቅፅል ቅርፅ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ ምግብ” ወይም “ትልቅ መጠን ያለው ምግብ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)