am_tn/psa/078/019.md

2.0 KiB

ተናገሩ

እስራኤላውያን ተናገሩ

በእውነት እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድ ለእኛ ማዘጋጀት ይችላልን?

ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ በእውነት እግዚአብሔር በምድረ በዳ ለእኛ ማእድ ሊያዘጋጅ ይችላል ብለን አናምንም!” ወይም “እግዚአብሔር፣ አንተ በእውነትም በምድረ በዳ ለእኛ ማእድ ማዘጋጀት የምትችል መሆንህን አረጋግጥልን!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ማእድ ማዘጋጀት

“ማእድ ማዘጋጀት” የሚለው ፈሊጥ ምግብ ለመብላት ማእድ ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ “ማእድ” የሚለው ለሚበላው ምግብ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምግብ አዘጋጀልን” (ፈሊጥ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ውሃ ተንዶለዶለ

ብዙ ውሀ በፍጥነት ወጣ

ነገር ግን እንጀራ መስጠት ይችላልን? ለህዝቡስ ስጋን ሊያቀርብ ይችላልን?

ህዝቡ በእነዚህ ጥያቄዎች እርሱን እየሰደቡ በእግዚአብሔር ላይ ይስቃሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን እንጀራ እንደሚሰጠንና ለህዝቡ ስጋ ማቅረብ እንደሚችል ይህን ሰርቶ እስከሚያሳይ ድረስ አናምንም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

አንጀራ… ስጋ

ከእፅዋት የሚገኝ ምግብ፣ ከእንስሳት የሚገኝ ምግብ፡፡ ምንም እንኳ ይህ ለሁሉም አይነት ምግብ ወካይ ቢሆንም የሚቻል ከሆነ በቀጥታ መተርጎም የተሻለ ነው፡፡ (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)