1.8 KiB
1.8 KiB
አጠቃላይ መረጃ፡-
ትይዩነት በዕብራውያን ግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)
የአሳፍ ትምህርት
“ይህ አሳፍ የፃፈው ትምህርት ነው፡፡” “የአሳፍ ትምህርት” የሚለውን መዝሙረ ዳዊት 50:1 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡
ትምህርት
ይህ የሙዚቃ ስልትን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ በ መዝሙረ ዳዊት 32:1 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡
ትምህርቴን ስማ
“ትምህርት” የሚለው ስም በግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ የማስተምርህን ስማ” ወይም “ሳስተምርህ ስማ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
የአፌን ቃላቶች
“አፍ” የሚለው ቃል ሰውየውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቃሌን” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)
አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ
“አፌን እከፍታለሁ” የሚለው ፈሊጥ መናገር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምሳሌ እናገራለሁ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
ስለ… ዘምሩ
“ተናገሩ፡፡” “ትናገራለች” የሚለውን በ መዝሙረ ዳዊት 19:2 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡
የተሰወሩ ነገሮችን
የአንተ ቋንቋ ሆን ተብሎ ለመረዳት አስቸጋሪ እንዲሆን የተደረጉትን አባባሎች የሚገልፅ ቃል ካለው እዚህ ላይ ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡