am_tn/psa/077/008.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

አሳፍ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠው መልስ ምን እንደሆነ እርግጠኛ ስላልነበረ ምናልባት በቀጥታ የተጠየቁ ጥያቄዎች ሊሆኑ ይችላሉ ስለዚህ በቀጥታ ሊተረጎሙ ይገባል፡፡

የኪዳኑ ታማኝነት ለዘላለም ጠፋ ወይ?

አሳፍ እግዚአብሔር ለኪዳኑ በታማኝነት ከእንግዲህ ወዲህ ስላለመስራቱ ሲናገር የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት እንደጠፋ አድርጎ ገልፆታል፡፡ ታማኝነት የሚለው ረቂቅ ስም በቅፅል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ለኪዳኑ ታማኝ መሆን ለዘላለም አቆመን?” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ቸርነቱን ረሳን? ከቁጣው የተነሳ ርህራሄውን ነፈገ?

እነዚህ እግዚአብሔር ርህራሄ አለማሳየቱን ተመሳሳይ ሀሳብ የሚያብራሩ ሁለት መግለጫዎች ናቸው፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከቁጣው የተነሳ ርህራሄውን ነፈገ?

አሳፍ ስለ ቁጣ ሲናገር ቁጣ ሌላ ሰው፣ ርህራሄ የሚባል፣ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ለመጠበቅ በር የሚዘጋ ሰው እንደሆነ አደርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር በእኛ ላይ ከመቆጣቱ የተነሳ ርህራሄ ለእኛ ማሳየቱን አቆመን?” (ሰውኛ ዘይቤ እና መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)