am_tn/psa/075/007.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

አሳፍ ስለ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡

እርሱ ያዋርዳል፣ እርሱ ያከብራል

የግሱ ተሳቢ በግልፅ ሊብራራ ይችላል፡- “እርሱ አንዳንድ ሰዎችን ያዋርዳል፣ ሌሎች ሰዎችን ደግሞ ያከብራል፡፡ “ያዋርዳል” እና “ያከብራል የሚሉት ቃላቶች እግዚአብሔር ሰዎችን ባለስልጣን ስለማድረግና የሰዎችን ስልጣን ስለመውሰዱ ተለዋጭ ዘይቤዎች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ አንዱን ሰው በሌላ ሰው ምትክ ንጉስ ያደርገዋል” ወይም “እርሱ የአንዱን ሰው ስልጣን ይወስድና ለሌላው ሰው ስልጣን ይሰጠዋል ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ የሞላበት ፅዋ… በቅመማ ቅመም የተቀመመ

እግዚአብሔር ሰዎችን ሲቀጣ ሰዎቹ ጠንካራ ወይን ጠጅ እንደጠጡና እንደታመሙ ሰዎች ይሆናሉ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ

ዐረፋ ሰዎች እንዲሰክሩ ለሚያደርገው የወይን ጠጅ ጥንካሬ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠንካራ የወይን ጠጅ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅመማ ቅመም

የደረቁ ቅጠላ ቅጠሎች ወይም መሬት ውስጥ የሚገኙ ዘሮች

ገለበጠው

ከትልቅ ፈሳሽ መያዣ ሰዎቹ ወደሚጠጡበት ፅዋዎች ገለበጠው

እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ጠጡት

“እያንዳንዱን የወይን ጠጅ ጠብታ ጠጧት”