am_tn/psa/075/004.md

3.7 KiB

አመፀኞችንና ክፉዎችን… እላቸዋለሁ

አመፀኞች እና ክፉዎች የሚሉት ቃላቶች የስም ቅፅሎች ሲሆኑ በስም ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ ለሁለተኛው ሀረግ የሚያስፈልገው ግስ ከመጀመሪያው ሀረግ ሊወስድ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለአመፀኞች ሰዎች… አልኋቸው… ለክፉዎች ሰዎች… አልኋቸው” (የስም ቅፅሎች እና አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

አልሁ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) እግዚአብሔር እየተናገረ ነው ወይም 2) አሳፍ እየተናገረ ነው፡፡

አመፀኞች አትሁኑ… አታንሱ… የአንተን ወደ ላይ አታንሳ… አትናገር

ተናጋሪው ለብዙ ክፉ ሰዎች እተናገረ ነው ስለዚህ እነዚህ ቅርፆች ሁሉም ብዙ ቁጥር ናቸው፡፡ (ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ቀንድህን ወደ ላይ አታንሳ

አሳፍ ስለ ክፉ ሰዎች ሲናገር በራሳቸው ላይ ቀንድ እንዳላቸው፣ አንገታቸውን እንደሚመዝዙና ሌሎች እንስሳትን ለማስፈራራት ራሳቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው እንደሚያነሱ እንስሳት አድርጎ ገልጧቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በራሳችሁ አትተማመኑ” ወይም “እንዴት ብርቱ ነኝ እያላችሁ በራሳችሁ አትመኩ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀንድህን ወደ ከፍታዎች አታንሳ

አሳፍ ስለ ክፉ ሰዎች ሲናገር ነራሳቸው ላይ ቀንድ እንዳላቸው፣ አንገታቸውን እንደሚመዝዙና ሎለሎች እንስሳትን ለማስፈራረራት ቻሉትን ያህል ራሳቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው እንደሚያነሱ እንስሳት አድርጎ ገልጧቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ በተለይም ደግሞ ከእግዚአብሔር በላይ ትልቅ እንደሆናችሁ በማሰብ ራሳችሁን ከፍ እንዳታደርጉ እርግጠኞች ሁኑ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በትዕቢተ በተሞላ አንገት

አሳፍ እግዚአብሔርን ስለሚቃወሙና ስለሚገዳደሩ ክፉ ሰዎች ሲናገር በራሳቸው ላይ ቀንድ እንዳላቸው፣ አንገታቸውን እንደሚመዝዙና ሌሎች እንስሳትን ለማስፈራራት ራሳቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርው እንደሚያነሱ እንስሳት አድርጎ ገልጧቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በትዕቢት” (ፈሊጥ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ክብር ከምስራቅ… አይመጣም

አሳፍ ራሱን ከፍ ስለሚደርግ ሰው ሲናገግ ራሱ ሰውየው ከፍ የማድረግ ተግባር እንደሆነ አድርጎ ገልፆታል፡፡ በተጨማሪ እርሱ እግዚአብሔር ለሰው ብርታትና ክብር ስለመስጠቱ ሲናገር እግዚአብሔር ሰውየውን በአካል ወደ ላይ ከፍ እንዳደረገው አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን ወደ ላይ ከፍ የሚያደርግህ ከምስራቅ የሚመጣ ሰው አይደለም” ወይም “አንተን ብርቱ የሚያደርግህና ሰዎች እዲያከብሩህ የሚያደርግህ ከምስራቅ የሚመጣ ሰው አይደለም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)