am_tn/psa/074/022.md

1.4 KiB

ለክብርህ ተሟገት

“አንተ ፃድቅ እንደሆንህ ለሁሉም አሳይ”

አስብ

“ትኩረት ስጥ፡፡” እግዚአብሔር ሞኞች እርሱን እንደሚሰድቡት አልረሳም ነገር ግን ስለዚህ ነገር እርሱ የሚያስብ አይመስልም፡፡ ይህ በ መዝሙረ ዳዊት 2 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡

የባላጋራዎችህ ድምፅ

ድምፅ የሚለው ቃል ሰዎች ሲናገሩ ለሚጠቀሙባቸው ቃላቶች ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአንተ ጠላቶች የሚናገሩት ነገር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ወይም በማያቋርጥ ሁኔታ የሚቃወሙህ ሰዎች ሁካታ

ዘማሪው እግዚአብሔርን ስለሚቃወሙት ሰዎች ቃላቶች ሲናገር ከእንስሳት ወይም እንደ ውሃና ነፋስ ከመሳሰሉ ሕይወት የሌላችው ቁሳቁሶች የሚወጣ ከባድ ጩኸት እንደሆኑ አድርጎ ገልጾታል። አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ያለማቋረጥ በአንተ ላይ የሚቃወሙ ሰዎች ጩኸትና ትርጉም አልባ ቃላቶችን ትኩረት ስጥ” (አስጨምሬ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ተቃውሞ

በድፍረት መቃወም