am_tn/psa/074/020.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

አሳፍ ለእግዚአብሔር የሚያደርገውን ልመና ቀጥሏል፡፡

የምድሪቱ የጨለማ አካባቢዎች የአመፅ ስፍራ ተሞልተዋል

አሳፍ ስለ አካባቢዎች ሲናገር አንድ ሰው የአመፅ ስፍራዎች ሊያስቀምጥበት እንደሚችለው ማስቀመጫ እቃ እንደሆኑ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አመፀኞች ሰዎች በምድር ዙሪያ በሚችሉት ቦታ ሁሉ በጨለማ ስፍራ ክፉ ድርጊት ይሰራሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የምድሪቱ የጨለማ አካባቢዎች

“ጨለማ” የሚለው ቃል ምናልባት መጥፎ ነገሮች ለሚፈፅሙት ስፍራ ወይም እስራኤላውን ለግዞት ተልከው ለነበሩበት ምድር ተለዋጭ ዘይቤ ነው ነገር ግን እነዚህ ቃላቶች የሚቻል ከሆነ በቁሙ ሊተረጎሙ ይገባል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የተጨቆኑት አፍረው አይመለሱ

“ክፉ ሰዎች የተጨቆኑትን እንዲያሸንፉና እንዲያሳፍሯቸው አታድርጋቸው”

የተጨቆኑት

እነዚህ በሀይለኛ ሰዎች በጭካኔ የሚሰቃዩ ሰዎች ናቸው፡፡

ድሆችና የተጨቆኑ

“ድሆች” እና “የተጨቆኑ” የሚሉት ቃላቶቸ በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን እግዚአብሔር የእርሱን እርዳታ የሚፈልጉትን ሰዎች እንደሚያድን አፅንኦት ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ ቃላቶች በ መዝሙረ ዳዊት 35:10.ላይ እንዴት እንደተተረጎሙ ተመልከት፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)