am_tn/psa/073/023.md

1.0 KiB

እኔ ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነኝ

እዚህ ላይ “እኔ” የሚለው ቃል የሚወክለው አሳፍን ነው፡፡ እዚህ ላይ “አንተ” የሚለው ቃል ደግሞ የሚወክለው እግዚአብሔርን ነው፡፡

አንተ ቀኝ እጄን ያዝከኝ

የሰው “ቀኝ እጅ” የሰውን ሁለንተና ያመለክታል፡፡ ይህ ፅናትና ዋስትና የሚሰጠውን ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ፅኑ አብሮነት የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ አጥብቀህ ያዝከኝ” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ክብርህ ተቀበለኝ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) “ሰዎች በሚያከብሩኝ ስፍራ አስቀምጠኝ” ወይም 2) “አንተ ወዳለህበት እኔን በመውሰድ አክብረኝ፡፡” “ተቀበለኝ” የሚለው በ መዝሙረ ዳዊት 49:15 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡