am_tn/psa/073/001.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት በዕብራውያን ግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

የአሳፍ መዝሙር

“ይህ አሳፍ የጻፈው መዝሙር ነው፡፡” ይህ በ መዝሙረ ዳዊት 53:1 ላይ አንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡

እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ

ዘማሪው የሚናገረው እግዚአብሔርን መታመን አንዳልቻለና በሚያዳልጥ መንገድ ሲራመድ ሊወድቅ እንደደረሰ አድርጎ ራሱን በማሰብ ሀጢአት ለመስራት እንደፈለገ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በእግዚአብሔር መታመን ለማቆም ደርሼ ነበር፤ በእርሱ ላይ ትልቅ ሀጢአት ለመስራትና በደለኛ ለመሆን ደርሼ ነበር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በአመፀኞች ቀንቼ ነበር

“አመፀኞች ቀናሁባቸው” ወይም “አመፀኞች ሰዎች የነበራቸው መልካም ነገር እንዲኖራቸው አልፈልግም”

አመፀኞች

“አመጸኞች” የሚለወ ቅፅል እንደ ስም ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አመፀኞች ሰዎች” (የስም ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)

የክፉዎች ባለጠግነት

“ባለጠግነት” የሚለው ቃል እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉዎች በጣም ብዙ መልካም ነገር እንዳላቸው አይቼ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉዎች

“ክፉዎች” የሚለው ቅፅል እንደ የስም ሀረግ ሊተረጎም ይቸላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች” (የስም ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)